አዲስ ኢንተርናሽናል ባንክ አክስዮን ማህበር
የዳሬክተሮች ቦርድ አባላት ዕጩዎችን ስለመጠቆም የወጣ ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ባወጣው መመሪያ መሰረት የባንካችን የዳሬክተሮች ቦርድ አስመራጭ ኮሚቴ በባንኩ የባለአክስዮኖች 7ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ መመረጡ ይታወሳል፡፡

በዚሁ መሰረት ኮሚቴው የዳሬክተሮች ቦርድ ዕጩ አባላትን ጥቆማ ከሰኔ 24 ቀን 2011 ዓ.ም ጀምሮ ይቀበላል፡፡ የጥቆማ መቀበያ ጊዜው እስከ መስከረም 23 ቀን 2012 ዓ.ም :: በዚሁ መሠረት በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መመሪያ ቁጥሮች SBB/70/2019 እና SBB/71/2019 ላይ የተዘረዘሩትንና ከዚህ በታች የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ዕጩ የቦርድ አባላትን ከጊዜ ገደቡ በፊት ባለአክሲዮኖች እንድትጠቁሙ ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡

ለዳይሬክተሮች ቦርድ ዕጩ አባልነት የሚጠቆሙ ባለአክስዮኖች ሊያሟሉ የሚገባቸው መስፈርቶች

  1. የባንኩ ባለአክስዮን የሆነ፣
  2. ዕድሜው 30 ዓመትና ከዚያ በላይ የሆነ፣
  3. የማንኛውም ባንክ ሠራተኛ ያልሆነ፣
  4. ሀቀኛ፣ታማኝ እና መልካም ዝና ያለው፣ በእምነት ማጉደል፣ትክክለኛ ያልሆነ የሂሳብ መግለጫ በማቅረብና በመሳሰሉት ተከሶ ፍርድ ቤት የጥፋተኝነት ውሳኔ ተሰጥቶበት የማያውቅ፣
  5. በሌላ የፋይናንስ ድርጅት የቦርድ አባል ወይም ዋና ስራ አስፈፃሚ ያልሆነ፣
  6. በንግድ ሥራ አስተዳደር፣በኢኮኖሚክስ፣ሂሳብ አያያዝ፣በፋይናንስና በተመሣሣይ ዘርፎች ቢያን የመጀመሪያ ዲግሪ ያለውና ቢቻል በባንክ ሥራ የሥራ ልምድ ያለው
  7. በራሱ ወይም በሚመራው ወይም ሥራ አስኪያጅ በሆነበት ድርጅት ላይ የሙስና ክስ ያልተመሰረተበት፣
  8. በኪሣራ ምክንያት ንብረቱ ለዕዳ ማካካሻ ያልተወሰደበት፣
  9. የባንክ ብድር ባለመክፈሉ ምክንያት ንብረቱ በሀራጅ ያልተሸጠበት፣ ተከሶ ያልተፈረደበት ወይም እሱ የሚመራው ወይም ሥራ አስኪያጅ የሆነበት ድርጅት ወይም የገንዘብ ተቋም የተበደረውን ገንዘብ ባለመክፈሉ ብድሩ ወደ ጤናማ ያልሆነ የብድር ደረጃ ያልዞረበት፣
  10. በቂ ገንዘብ ሳይኖ በደረቅ ቼክ ሂሳቡ ያልተዘጋበት፣
  11. ታክስ ባለመክፈል ተከሶ ጥፋተኛ ያልተባለ፣
  12. ሌሎች በብሔራዊ ባንክ መመሪያዎች የተገለፁ መስፈርቶችን የሚያሟሉ መሆን አለባቸው፡፡
  13. የቦርድ አመራሩን ቀጣይነት ለማረጋገጥ ሲባል ከነባር የቦርድ አባላት መካከል ሁለት የአገልግሎት ዘመን ወይም ስድስት ዓመታት ያገለገሉት ሊጠቆሙ ይችላሉ ፡፡

ማሳሰቢያ፡-

  1. በተባዕታይ ፆታ የተገለፀው ለአነስታይ ፆታም ይውላል፡፡
  2. ጥቆማውን ከባምቢስ ሱፐርማርኬት ከፍ ብሎ ኖክ የነዳጅ ማዲያ ፊት ለፊት በሚገኘው ዝቋላ ኮምኘሌክስ ህንፃ አዲስ አንተርናሽናል ባንክ አ.ማ የአክስዮን አስተዳደር ጽ/ቤት ገቢ ማድረግ ወይም በመልዕክት ሣጥን ቁጥር 2455 አ.አ “ለአዲስ ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ የዳሬክተሮች ቦርድ አስመራጭ ኮሚቴ ጽ/ቤት” በመላክ ማቅረብ ይቻላል፡፡
  3. ለጥያቄና ማብራሪያ በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 0115-57-05-06 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
  4. ከመስከረም 23 ቀን 2012 ዓ.ም በኋላ የሚቀርቡ ጥቆማዎች ተቀባይነት የሌላቸው መሆኑን ከወዲሁ በአክብሮት እናስታወቃለን፡፡

የዳሬክተሮች ቦርድ አስመራጭ ኮሚቴ
አዲስ ኢንተርናሸናል ባንክ አ.ማ
ሰኔ 24 ቀን 2011 ዓ.ም